የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

57
ባሕር ዳር:መጋቢት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የ2023 የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ዓመታዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ መጀመሩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በጉባኤው ለአፍሪካ አባል ሀገራት ኤጀንሲው የሚያደርገውን ድጋፍና የቴክኒካዊ ትብብር አተገባበር ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።
በጉባዔው ላይ የኤጀንሲው ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የአባል ሀገራት ተወካዮችና፣ የአፍሪካ ሀገራት የዘርፉ የምርምርና የድጋፍ ብሔራዊ አሥተባባሪዎች መገኘታቸው ተጠቁሟል።
ጉባዔው ከመጋቢት 4 እስከ 8/2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት አመራሮች ፣ የዞን ባለሙያዎች እና የጤና ተቋማት ኀላፊዎች በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን ጎበኙ።
Next article“ወጣቶች ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና መሠረት መኾን አለባቸው” ዶክተር ጋሻው አወቀ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ።