
ባሕር ዳር: መጋቢት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) UNWTO በጎጃም የሚገኘውን የጮቄ ተራራ ኢኮ ቱሪዝም ልማት የዓለም ድንቅ ቱሪዝም መንደር ውድድር አሸናፊ አድርጎ መርጧል::
ሽልማቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ከጮቄ ሙሉ ኢኮ ሎጅ ተወካዮች ጋር በመሆን በሳውዲ አረቢያ አሉላ ከተማ ከUNWTO ሴክሬታሪ ጀኔራል ተቀብለዋል።

የUNWTO ሴክሬታሪ ጀኔራል በውድድሩ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 ሀገራት በላይ እና ከ100 በላይ የቱሪዝም መዳረሻዎች የተሳተፉ ሲሆን ማኅበረሰቡን ያሳተፉ እና ዘላቂ የሆኑትን ሸልመናል ብለዋል።
በዚህ ደማቅና አኩሪ መርኃ ግብር ላይ በሳውዲ ሀገር የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ መገኘታቸውም ታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!