አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳይ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ።

141
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አምባሳደሯ በኢትዮጵያ እና በኅብረቱ መካከል ያለውን ግንኙነት በአዲስ መልክ ማደስ በሚቻልበት ላይ መክረዋል።
በቤልጂየም፣ ሉክሰምበርግ እና የአውሮፓ ኅብረት ተቋማት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳይ ምክትል ዋና ጸሐፊ ኤነሪኬ ሞያ ጋር ውይይት አደረጉ።
የውይይታቸው ትኩረትም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በኅብረቱ መካከል ያለውን ግንኙነት በአዲስ መልክ ማደስ በሚቻልበት ላይ መክረዋል።
አምባሳደር ሂሩት ስለ ሽግግር ፍትሕ ማዕቀፍ፣ የሰላም ስምምነቱ አሁን ያለበትን ደረጃ እና የሀገራዊ ምክክር ዝግጅትን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳይ ምክትል ዋና ጸሐፊ ኤንሪኬ ሞራ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በቅርብ ለመከታተል ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በሚቀጥለው ሳምንት በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በሀገሪቷ መሬት ያለውን እውነታ ለማወቅ እንደሚያግዛቸው መግለጻቸውን በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ አዘጋጅነት በትብብር ሥልጠና አተገባበር ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ክልል አቀፍ የምምክክርና ንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሔደ ነው።
Next articleለሽግግር ፍትህ ውጤታማነት በመድረኮች በመገኘት ዜጎች የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡