በአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ አዘጋጅነት በትብብር ሥልጠና አተገባበር ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ክልል አቀፍ የምምክክርና ንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሔደ ነው።

69
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ልማት ለዘላቂ የሥራ እድል ፈጠራ” የመድረኩ መሪ መልእክት ነው።
መድረኩ እንደ ሀገርም ኾነ እንደ ክልል ለዘላቂ የሥራ እድል ፈጠራ ሥራው ማነቆ የኾኑ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩና መፍትሔ አመላካች ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል።
በተላይም የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ትብብራዊ ቅንጅት ለክኅሎት ልማትና ዘላቂ የሥራ እድል ፈጠራ ላይ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት እንደሚደረግባቸው ነው ከመርሃግብሩ ለመረዳት የተቻለው።
በምክክር መድረኩ የፌደራል፣ የክልልና የዞን የሥራ ኀላፊዎች፣ ተጋባዥ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች ይሳተፉበታል ተብሏል።
አሚኮ ኦንላይን ጉዳዩን ተከታትሎ መረጃውን ያደርሳል።
ዘጋቢ፦ ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleኮሪያን ፋውንዴሽን ፎር ኢንተርናሽናል ኼልዝ ኬር በጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሶስትዮሽ የስምምነት ውል ተፈራረመ።
Next articleአምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት የፖለቲካ ጉዳይ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ።