ኮሪያን ፋውንዴሽን ፎር ኢንተርናሽናል ኼልዝ ኬር በጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሶስትዮሽ የስምምነት ውል ተፈራረመ።

111
አዲስ አበባ: መጋቢት 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ኮሪያን ፋውንዴሽን ፎር ኢንተርናሽናል ኼልዝ ኬር የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲና እና ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሶስትዮሽ የስምምነት ውል ተፈራርመዋል።
በስምምነቱ የተገኘው የ8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ነው።
በጦርነቱ ምክንያት የወደመውን የጤናውን ዘርፍ መልሶ ለመገንባት ያግዛል ተብሏል። ድጋፉ በተለይም በእናቶች፣ በህፃናትና በጨቅላ ህፃናት ዙሪያ ያሉ ተግባራትን ለማሻሻልና ለመሥራት ይውላል ተብሏል።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክ ዳይሬክተሩ ዶክተር አስማማው አጥናፍ የወደሙ ጤና ተቋማት መሰረታዊ ችግሮቻቸው እንዲፈቱ እንሠራለን ብለዋል።
የኮሪያን ፋውንዴሽን ፎር ኢንተርናሽናል ኼልዝ ኬር ግብረ ሰናይ ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቦክ ህዩን ናም በቀጣይም ከክልሉ ጋር በጋራ እንሠራለን ነው ያሉት።
May be an image of 6 people and people standing
የአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የተቋማት ውድመት እና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች የደረሱበት፤ መልሶ ለመገንባት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመኾኑ የኮሪያ ሕዝብና መንግሥት ከጎኑ ይቆማል ብለዋል ዳይሬክተሩ።
ኮሪያና ኢትዮጵያ ጥሩ ሀገራዊና ሕዝባዊ ግንኙነት አለን ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ሀገርም ይሁን በአማራ ክልል የጤናው ዘርፍ ለማገዝ ደስተኞች ነን ብለዋል።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክ ዳይሬክተሩ ዶክተር አስማማው አጥናፍ ችግሩ በክልሉ መንግሥት ብቻ የሚፈታ ባለመኾኑ በቀጣይም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጥምረት እንሠራለን ብለዋል።
ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የስማርት ሲቲ ትግበራን ዕውን ለማድረግ የነቃ አመራርና ስልጡን ማኅበረሰብ መፍጠርን ይጠይቃል” ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ዴኔሮ
Next articleበአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ አዘጋጅነት በትብብር ሥልጠና አተገባበር ላይ ያተኮረ ከፍተኛ ክልል አቀፍ የምምክክርና ንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሔደ ነው።