
ባሕርዳር: መጋቢት 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ተመድ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር በቀጣናው ሠላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ መኾኑን የተመድ ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ሃና ቴቴህ ገለጹ።
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተመድ ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ሃና ቴቴህ ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሪቶሪያውን የሰላም ሥምምነት ለመተግበር እያደረገ ያለውን አበረታች ጥረት በተመለከተ ለልዩ መልእክተኛው ማብራሪያ መሥጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!