
✍️”የአማራ ክልል አሁን ላይ የተረጋጋ ነው” ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
✍️በአማራ ክልል ለመልሶ መቋቋም ሥራ 1 ቢሊዮን ብር ተመድቦ እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መሥተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ።
✍️አርሶ አደሮች የካሳ ክፍያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት የሚያደርግ ተቋም ለማዋቀር እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ተናገሩ።
✍️በሕግና ሥርዓት ያልተመራ የገበያ ሥርዓት በመኖሩ የዋጋ ንረቱ ከፍ ማለቱን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ(ዶ.ር) ተናገሩ።
✍️ለቀናት ሲካሄድ የቆዬው የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ ተጠናቀቀ።
✍️ባለፉት ስድስት ወራት በግብርናው ዘርፍ አበረታች ለውጦች መታየታቸውን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
✍️”ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር በቀጣናው ሠላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ ነው” ሃና ቴቴህ
✍️”የኢትዮጵያ ምርቶች በቻይና ገበያ ተደራሽነታቸውን ለማስፋት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ” በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ
✍️”የፖለቲካ ፓርቲዎች በሽግግር ፍትሕ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን አለባቸው” የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
✍️”በአማራ ክልል 16 ሚሊዮን የሚሆነውን ሕዝብ በጤና መድኅን ማሳተፍ ተችሏል” የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ መልካሙ አብቴ (ዶ.ር)
✍️”የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ያስችላል” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
✍️የባሕር ዳር ከተማን የውኃ አቅርቦት ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ አስታወቀ።
✍️”ዘመኑ የዲጅታል ነው እና ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት አሠራሮቻችን ሁሉ ዘመኑን የዋጁ ማድረግ ያስፈልጋል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)
✍️”የስማርት ሲቲ ትግበራን ዕውን ለማድረግ የነቃ አመራርና ስልጡን ማኅበረሰብ መፍጠርን ይጠይቃል” ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል ዴኔሮ
✍️14 የፈረስ ጉልበት ያለውና በቀን ከአንድ ሄክታር በላይ መሬት እንደሚያርስ ተስፋ የተጣለበት የእርሻ መሣሪያ በሀገር ውስጥ ምርት አሻሽሎ ማቅረቡን የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቀ፡፡
✍️የሰዴ ሙጃ እና የስማዳ ወረዳ ነዋሪዎች በራሳቸው አቅም እየሠሩት ላለው መንገድ መንግሥት ድልድይ እንዲገነባላቸው ጠየቁ፡፡
✍️በበለስ-ደብረማርቆስ- ሱሉልታ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ የስርቆት ወንጀል ጉዳት ደረሰ።
✍️ኮሪያን ፋውንዴሽን ፎር ኢንተርናሽናል ኼልዝ ኬር በጦርነት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሶስትዮሽ የስምምነት ውል ተፈራረመ።
✍️ከበጋ መስኖ ስንዴ 70 ሺህ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱን የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።
✍️”የበልግ ዝናብን በተገቢው መልኩ በመጠቀም የግብርና እንቅስቃሴን ማፋጠን ይገባል” የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!