በወረኢሉ ወረዳ የባዮጋዝ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ልምድ እየተጎበኘ ነው፡፡

452

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 20/2012 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ውኃ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ከፍተኛ መሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተካተቱበት ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

በወረኢሉ ወረዳ በአማራጭ ታዳሽ የኃይል ምንጭነት የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ አርሶ አደሮች ልምድ ነው እየተጎበኘ የሚገኘው፡፡ የአርሶ አደሮችን የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልምድ ለመቀመር የሚያስችል ግብዓት ለማግኘት የሚያስችል ጉብኝት መሆኑም ታውቋል፡፡

ሀገር አቀፍ መረጃዎች እንደሚያሳዩት 56 ከመቶ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ኃይል እያገኙ አይደሉም፤ እንደ ባዮ ጋዝና የፀሐይ ብርሃንን የሚሰበስቡ መሳሪያዎች (ሶላር ፕሌትስ) ያሉ አማራጭ ታዳሽ የኃይል ምንጮች ችግሩን ለመቅረፍ ትኩረት የተደረገባቸው ናቸው፡፡

ዘጋቢ፡- ቤተልሔም ሰሎሞን ከወሎ ኤፍ ኤም

Previous articleባለፈው ሩብ ዓመት ብቻ 1ሺህ 221 ፈቃደኛ ኢትዮጵውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
Next articleየሐዲስ ዓለማየሁ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት ሥራ ጀምሯል፡፡