ወጣቱ ከግጭት ተግባር ተቆጥቦ በፍሬያማ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስምሪት ላይ ማተኮር እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ፡፡

152

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 20/2012 ዓ.ም (አብመድ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ይህንን ያሉት በሸራተን አዲስ ሆቴል ሀገር አቀፍ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ ጉባኤን ባስጀመሩበት ጊዜ ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ወጣቶች ከግጭት ዓውድ መውጣት እንደሚገባቸውና በውጤታማ ሥራ ዕድል ፈጠራ ስምሪት ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ መንግሥትም ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር አስቻይ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻችም ነው አቶ ደመቀ ያመለከቱት፡፡

ምንጭ፡- የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

Previous articleየአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት 24 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ለመንግሥት አሥመለሰ፡፡
Next articleባለፈው ሩብ ዓመት ብቻ 1ሺህ 221 ፈቃደኛ ኢትዮጵውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡