የአማራ ክልል ምክር ቤት የሁለተኛ ቀን የከሰዓት ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

111
ባሕር ዳር: የካቲት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 6ኛው ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔው የሁለተኛ ቀን የከሰዓት ጉባዔውን እያካሄደ ነው።
በጉባዔው ላይ በቋሚ ኮሚቴዎች የቀረቡ ሪፖርቶችን እና የውሳኔ ሀሳቦችን መነሻ በማድረግ የምክር ቤት አባላት ጥያቄዎችን እያነሱ ውይይት እየተደረገ ነው።

በውይይቱ ላይ የምክር ቤት አባላት በየአካባቢዎች ሥለሚገኙ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሂደት እና የልማት ሥራዎች እንቅስቃሴ እያነሱ ነው። የክልሉን ሕዝብ ሰላም በዘላቂነት ከማረጋገጥ አኳያ መሠራት ያለባቸውን ጉዳዮችም አንስተዋል።
ከቆይታ በኋላም አስፈጻሚ እካላት በውይይቱ ላይ ለተነሱ ጉዳዮች ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከብሪታንያ እና ሰሜን አየርላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።
Next articleአዲሱ የባሕር ዳር አባይ ወንዝ ድልድይ አኹናዊ ገጽታ