አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከብሪታንያ እና ሰሜን አየርላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።

89
ባሕር ዳር:የካቲት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከብሪታንያ እና የሰሜን አየርላንድ አምባሳደር ዳረን ጆን ዌልች ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ ብሪታንያ በኢትዮጵያ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡
May be an image of 6 people, people sitting, people standing, office and indoor
ኢትዮጵያ በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗንም በዚህ ወቅት ገልጸዋል።
በግጭቱ ጉዳት በደሰረባቸው አካባቢዎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከማስጀመር ባለፈ የሽግግር ፍትሕ ፍኖተ ካርታ በመዘጋጀት ላይ ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበአማራ ክልል የተጀመሩ የጤና ተቋማት ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ አለመጠናቀቃቸውን የክልሉ ምክር ቤት የሰው ሃብት እና ቱሪዝም ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡
Next articleየአማራ ክልል ምክር ቤት የሁለተኛ ቀን የከሰዓት ጉባዔውን እያካሄደ ነው።