
ባሕር ዳር:የካቲት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 6ኛው ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬም ሲቀጥል በወልዲያ ከተማ የሚገኘው ሞሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም በጦርነት ወቅት የደረሰበት ጉዳት መጠገን እንዳለበት ምክር ቤቱ አሳስቧል።
የክልሉ ምክር ቤት ሴቶች ሕፃናት፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወልዲያ ስታዲየም በጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ኾኖ እንደሚገኝ ነው ያስረዳው።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ሀናን አብዱ መጫወቻ ሜዳው ጉዳት እንደደረሰበት ቢታወቅም ለመጠገን ግን የተደረገ ጥረት አለመኖሩን ለምክር ቤቱ አስገንዝበዋል። ሜዳው ወደቀደመ የስፓርት ማዕከልነቱ እንዲመለስ በተደራጀ ሁኔታ ጥገና ሊሠራለት እንደሚገባም ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!