
ባሕር ዳር:የካቲት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ፋብሪካው ትላንት የካቲት 29/2015 ዓ.ም ነጭ ስኳር ማምረት መጀመሩን አስታውቋል፡፡
በቀጣይም ፋብሪካው ወደ ላቀ የምርት ሂደት ውስጥ በመግባት የታለመውን ግብ ያሳካ ዘንድ ተገቢውን አመራር ለመሥጠት ዝግጁ መሆናቸውን የፋብሪካው የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ለዚህ ስኬት መድረስ እልህ አስጨራሽና ብዙ ውጣ ውረድ ላለፉ አካላት በተለይም ለመላው የድርጅቱ ሠራተኞች ፣ ለማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ለጃዊና አካባቢው ኀብረተሰብ በጣና በለስ ሥራ አመራር ቦርድ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!