
ባሕርዳር:የካቲት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC) 2023 ላይ ዕውቅና ተሰጣቸው።
ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ በትላንትናው ዕለት በተካሄደው “Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023” ላይ የተበረከተላቸውን “Women in Global Health Award” የዕውቅና ሽልማት በተወካያቸው በኩል ተቀብለዋል።
ዕውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም እና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራት እና ፍትሐዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሠሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።
ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ይህ ሽልማት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለ እና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ ዕውቅናውን ማግኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!