
ባሕርዳር: የካቲት 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔ ሲጀመር የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የአሥተዳደር ምክር ቤቱን የ2015 ዓ.ም የስድስት ወር አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ አንጻራዊ ሰላም እና መረጋጋት ቢፈጠርም አሁንም ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋትን በመፍጠር በኩል በትኩረት ሊሠራ የሚገባ መኾኑን አንስተዋል። የዜጎች ሞት እና መፈናቀል አለመቆሙ አሁንም ከስጋት እና ከችግር እንዳንወጣ አድርጓል ብለዋል።
ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት ለሌሎች የልማት እና የመልካም አሥተዳደር እቅዶች መሳካት ወሳኝ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ “በሀገርም ኾነ በክልል ደረጃ የገጠሙንን ችግሮች በሠላም እንዲፈቱ በትኩረት ይሠራል” ነው ያሉት።
ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ ፈታኝ እና ውስብስብ ችግሮች ቢያጋጥሙም የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ እና የክልሉን የመልማት ፍላጎት ታሳቢ ያደረጉ የልማት ሥራዎች በታቀደላቸው የጊዜ መርሐ ግብር እንዲጠናቀቁ እየተሠራ እንደኾነ አንስተዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!