የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ አደረገ።

82
ባሕርዳር:የካቲት 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ አደረገ።
አየር መንገዱ ወደ ዛንዚባር የሚያደረገውን በረራ ከዋና አብራሪዋ ጀምሮ ረዳት አብራሪ፣ የበረራ አስተናጋጆች እና ቴክኒሽያኖች ሴቶች ናቸው።
ከዚህም ባለፈ የአየር ትራፊክ፣ የበረራ ደህነነትና የጭነት ቁጥጥር፣ የበረራ መለኪያ እስከ አውሮፕላኑ መነሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተመራ ነው።
ይህ ሴቶች ያላቸው አቅም ሳይገደብ ማኅበረሰብን ማነፅ የሚችል አቅም እንዳላቸው ማረጋገጫ መሆኑን የአየርመንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
የዓለም የሴቶች ቀንን በማስመልከት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ በሴቶች የተመሩ በረራዎችን ሲያደርግ ይህ ለ7ኛ ጊዜ ሲሆን በረራው የአየርመንገዱ የመጀመሪያ ሴት አብራሪ በሆኑት ካፒቴን አምሳል ጓሉ የተመራ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የጾታ ዕኩልነትን ለማረጋገጥ በሀሳብ የበላይነት ማመን ያስፈልጋል” የአውራምባ ማኅበረሰብ መሥራች የክቡር ዶክተር ዙምራ ኑሩ
Next articleʺየድል ታሪክ መግለጫ፣ የነገሥታት መቀመጫ”