“የተሰጠንን ኃላፊነት ተጠቅመን የሕዝባችንን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ተግተን መሥራት ይገባናል!” ማተብ ታፈረ (ዶ.ር)

236

፨ደብረ ማርቆስ፡ የካቲት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ6 ወራት አፈፃፀም መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የደብረ ማርቆስ ከተማ ከንቲባ ይትባረክ፤ ደብረ ማርቆስ የምንመክርበት ይህ የትምህርት መድረክ ለቀጣይ ክልላዊ የትምህርት ልማት መሰረት እደሚሆንም ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው በበኩላቸው የመጪውን ጊዜ ስኬት የሚወስነው ዋነኛው ጉዳይ ትምህርት ላይ የምንሠራው ሥራ ነው ያሉ ሲሆን ነገን ውጤታማ ለማድረግ ዛሬ ላይ የምንሠራውን የትምህርት ዘርፍ ሥራን ለማሻሻል መትጋት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ትምህርት ላይ መሥራት ድህነትን በዘላቂነት ለማስወገድ እንደሚያስችል በማመን ማኅበረሰቡን በማስተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ የትምህርት ተቋማት የማስገንባት ሥራ እየተሠራ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አብርሃም ይህን ተግባር አጠናከሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ.ር) በመድረክ መክፈቻ ንግግራቸው የተሰጠንን ኃላፊነት ተጠቅመን የሕዝባችንን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ተግተን መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በየእርከኑ ያለን የትምህርት አመራሮች ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማስተባበር የሕዝባችንን ከፍታ የሚያረጋግጥ የትምህርት ስራ በመስራት ኃላፊነታችንን በአግባቡ ልንወጣ ይገባል ሲሉ ማተብ ታፈረ (ዶ.ር) ገልፀዋል። ፈተናዎችን አልፈን ውጤታማ የከፍታ ጉዞን ለማረጋገጥም ተማሪዎቻችን ላይ መሥራት አለብን።

ከአማራ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ኃላፊነቱን የማይወጣና ታሪካዊ ድርሻውን ለማሳለጥ የማይተጋ የትምህርት አመራርና ባለሙያ በትምህርት ተቋማት እንዲኖር አንፈቅድም ነው ያሉት ማተብ ታፈረ (ዶ.ር)።

በምሥራቅ ጎጃም ዞንና ደብረ ማርቆስ ከተማ ያገኘነው ተሞክሮም ተስፋ ሰጪ ጅምር ሥራዎችን ተመልክተናል፤
ለተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር መሻሻል ተደማምጠን በመሥራት ቁጭቶቻችንን ለመቋጨት በትብብር መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመድረኩ የክልል፣ ከተማ አስተዳደር እና የወረዳ አመራሮች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫዘሮች እንዲሁም የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ አመራሮች ተሳታፊ ናቸው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለ20 ወራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ መቸገራቸዉን የሐራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
Next article“ደሴ ከተማ ከምንጊዜውም በላይ የሕዝቦቿን እገዛ ትፈልጋለች” የደሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ