“ኢትዮጵያ በፓኪስታን ኢምባሲዋን በከፈተች በ6 ወር ውስጥ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ሥራ አከናውናለች፡፡” በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር

64

ባሕርዳር: የካቲት 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በፓኪስታን ኢምባሲዋን በከፈተች በ6 ወር ውስጥ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ሥራ ማከናወኗን በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ጀማል በክር ተናገሩ፡፡

80 የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቡደን ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋል ብለዋል።

አምባሳደር ጀማል በክር እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ሊኖራት የሚችለውን ተዕፅኖ ማሳደግ ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ በፓኪስታን ኢምባሲዋን የከፈተችው ከ6 ወር በፊት ነው ብለዋል።

ኢምባሲያችን በተከፈተ በአጭር ጊዜ ውስጥም በውኃ ዲፕሎማሲ ላይ የተስተካከለ እሳቤ እንዲኖር ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ኢትዮጵያ የትኛውንም ችግር የመፍታት አቅም እንዳላት የዲፕሎማሲ ሥራ መሠራቱን እና ከኢትዮጵያ ጎን እንዲኾኑ ማድረግ ስለመቻሉ አስረድተዋል። በአጭር ጊዜ ውስጥ በተሠራው ሥራም መልካም ተግባራትን ማከናወን ተችሏል ነው ያሉት።

በትልቁ የሠራነው ደግሞ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ነው ያሉት አምባሳደሩ በፈጠርነው ተቋማዊ ግንኙነት ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት፣ የንግድ እና የቱሪዝም አቅም አስረድተናል ። በዚህም የቀጥታ ኢንቨስትመንት እና የውጭ ንግዳችንን ማሳደግ በሚያስችል ግንኙነት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ከፓኪስታን ጋር የነበረውን የ78 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ የወጭ ንግድ ወደ 200 ሚሊዮን ለማድረስ አቅደን እየሠራን ነውም ብለዋል።

አሁን ላይ የንግድ ስምምነት ተደርጓል። የፓኪስታን የንግድ ሠዎችም ኢትዮጵያ መጥተው መሥራት የሚችሉበት ኹኔታ ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

የፊታችን እሁድ ከ80 በላይ የፓኪስታን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቡድን በኢትዮጵያ እንደሚመጣ የገለፁ ሲኾን ቡድኑ የግብርና፣ የጨርቃጨርቅ፣ የስፖርት፣ የኬሚካል፣ የማኑፋክቸሪንግ እንዲሁም በመድኃኒት እና የቀዶ ጥገና ቁሳቁሶች ማምረቻና በሌሎች የሚሳተፉ ዘርፎች የሚሳተፉ ባለሀበቶች ናቸው ተብሏል።

በኢትዮጵያ ያለው የሰው ኃይል አቅርቦት፣ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና እንዲሁም የአንድ መስኮት አገልግሎት ኢትዮጵያ ባለሃብቶሽን እንድትስብ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል አምባሰደሩ ጀማር በክር።

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article127ኛው የዓድዋ ድል በዓል አስመልክቶ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ
Next article“ዝክረ ዓድዋ በዓመት አንድ ቀን ብቻ ሳይኾን ዘላቂ ሀገራዊ እሴት እንዲኾን የብዙሃን መገናኛ ተቋማት መሥራት ይጠበቅባቸዋል” ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ