“ጥቁር ከሰውነት ያነሰ ነው፣ ሰለዚህም ሀገር መምራት አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ የቀበረው ዓድዋ ነው” የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ፡፡

85

“ጥቁር ከሰውነት ያነሰ ነው፣ ሰለዚህም ሀገር መምራት አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ የቀበረው ዓድዋ ነው” የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ፡፡

ኮምቦልቻ :የካቲት 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 127ኛው የዓድዋ በዓል በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር በድምቀት ተከብሯል፡፡
በኮምቦልቻ ከተማ በተከበረው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የአባቶችን አኩሪ ገድል ለመዘከር ወጣቶች በባዶ እግራቸው የእግር ጉዞ አካሂደዋል፡፡ በጉዞውም አባት አርበኞችን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በዓሉ በፉከራ፣ ቀረረቶ እና ሽለላ የታጀበም ነበር፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች ከዓድዋ የምንማረው አንድነትን ነው ብለዋል፡፡ ሕዝባችን ልክ እንደ ትናንቱ ዛሬም አንድ በመኾን ሀገሩን ከውስጥ እና ከውጭ ጠላት መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድ አሚን የሱፍ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት ዓድዋ የሁሉም ጥቁር ሕዝብ በዓል ነው ብለዋል፡፡ ዓድዋ ጥቁር ከሰውነት ያነሰ ነው፣ ሰለዚህም ሀገር መምራት አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ የቀበረ ነውም ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አበሻ አንለይ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck

Previous articleየአሁኑ ትውልድ እንደ ቀደምት አባቶቸ ሁሉ የሀገር ፍቅርን፣ ጀግንነትንና አንድነትን በመመሥረት ኢትዮጵያን ማጽናት እንደሚጠበቅበት ተገለጸ፡፡
Next article“ለቃሉ የሚያድር መሪ የሕዝቡን ልብ ይገዛል፤ በአንድ ጥሪም ይደማመጣል”” የታሪክ ምሁር አሰፋ ባልቻ (ዶ.ር)