የማዕከላዊ ጎንደር ዞን እና የወልቃይት ጠገዴ ስቲት ሁመራ ዞኖች የዓድዋ ድል በዓልን በጋራ እያከበሩ ነዉ።

193

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን እና የወልቃይት ጠገዴ ስቲት ሁመራ ዞኖች የዓድዋ ድል በዓልን በጋራ እያከበሩ ነዉ።

ሁመራ :የካቲት 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዓሉ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ማክሰኞ ገቢያ ትፋሻ ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ምጭዊ የተባለ ቦታ ነዉ እየተከበረ የሚገኘዉ።

ምጭዊ ጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያን ለመዉረር ሙከራ ያደረገበት ስፍራ ነዉ።

እዚህ ቦታ ላይ ከ 500 በላይ የ ፋሽስት ጣልያን ሰራዊት በረግረጋማው ቦታ ሰምጠዉ መቅረታቸዉን እና በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊት መደምሰሳቸዉን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ አቤል መብት ተናግረዋል።

በዓሉ በዚህ ቦታ መከበሩ የ አባቶቻችን ብልሃት እና ጀግንነት ለትዉልዱ ለማስተማር ነዉ ብለዋል።

ይን ስፍራ የቱሪስት መዳረሻ ቦታ ለማድረግ እየተሰራ መኾኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አሥተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለዉ ዓድዋ ላይ ያሸነፍነዉ ዘረኝነት ዛሬ በዉስጣችን እኛን መልሶ እየፈተነን ፣ እርስ በርስ እያጠፋፋን ፣ ኢትዮጵያንም እንደ ሀገር እያደማት ነዉ ብለዋል።

የዓድዋ ድል የፖለቲካ አቋም የሚራመድበት ሳይሆን የጥቁር ሕዝቦች የኩራት ምንጭ የሆኑት እነ አጼ ምኒልክ ፣ እቴጌ ጣይቱ እና በዘመኑ የነበሩ ጀግኖች አባቶቻችን የሚዘከሩበት የ ሀገር ፍቅር ስሜት የምንማርበት ፣ የአመራር ጥበብ የምንቀስምበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

127ኛዉ የዓድዋ ድል በዓሉ እየተከበረ የሚገኘዉ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ አስተባባሪነት ነዉ።

ዘጋቢ፦ አዲስ አለማየሁ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck

Previous article“ለቃሉ የሚያድር መሪ የሕዝቡን ልብ ይገዛል፤ በአንድ ጥሪም ይደማመጣል”” የታሪክ ምሁር አሰፋ ባልቻ (ዶ.ር)
Next article“የዓድዋ ድል የሚነግረን ብስለትን፣ ማስተዋልን፣ ጀግንነትን እና ታሪክን የማስቀጠል ትሩፋትን ነው” የሙሉዓለም የባሕል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር