
ባሕር ዳር:የካቲት 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዓሉ በእግር ጉዞ ፣ በፈረስ ትርዒቶች እና በኪነ ጥበባዊ ክንዋኔዎች ተከብሯል። በአከባበሩ ላይ የተገኙት የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በዓድዋ ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላም ጊዜ ጀግና ገበሬ በጦርነት ጊዜ ጀግና ተዋጊ መሆኑን ያሳየበት ነው ብለዋል።
የዓድዋ ድል ለጋራ ታሪካችን በአንድነት የተዋደቅንበት፣ የዛሬውን መልካችንን የያዝንበት በመሆኑ አንድነታችንን በሚያጎለብት መልኩ ሊከበር ይገባዋል ብለዋል።
ይህንኑ የድል ቀናችንን ለቀጣይ ድል ስንቅ አድርገን ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉም አቶ ሳሙኤል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎችም ዓድዋ ዛሬ ላይ ቀና ብለን እንድንሄድ ያደረጉን አያቶቻችን አኩሪ ታሪክ በመሆኑ እያከበርነው እንገኛለን ብለዋል። አሁን ያለው ትውልድም የአባቶቹን አደራ በመጠበቅ ታሪኩን ለትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅበታል ብለዋል።
ዘጋቢ ፦ ተመስገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!