
ባሕር ዳር: የካቲት 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ በዓሉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ኅላፊነቱን በባለቤትነት ይዞ እንዲሠራ በመንግሥት በኩል መወሰኑ ተገቢ እና ትክክለኛ ነበር ያሉት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻ ብርሃኑ ጁላ ናቸው፡፡
በዓሉን በተሰጠን ኅላፊነት ልክ ለመሥራት ሞክረናል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ሁላ “በቀጣይ ዓመት የዓድዋ ድል በዓልን አፍሪካዊ ወንድሞቻችን አካትተን አፍሪካዊ ክብረ በዓል ለማድረግ እንሠራለን” ብለዋል፡፡
ድሉ አፍሪካ ከባርነት ነጻ እንድትወጣ ፈር የቀደደ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ የዚህ ትውልድ ሠላም አስከባሪ ሆነን በተሠማራንባቸው ቦታዎች ሁሉ ከዓድዋ ድል ባለቤት ሀገር በመሄዳችን የተለየ ክብር እና አቀባበል ይደረግልናል ነው ያሉት፡፡ ሠራዊቱም ታሪኩን በሚመጥን መልኩ ግዳጁን በጽናት የሚወጣ ሠራዊት ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
የዚህ ዘመን ሠራዊት በአባቶቹ ጽናት እና ሀገራዊ አንድነት የተመሠረተ ሠራዊት ነው ያሉት ኢታማዦር ሹም በላቀ ግዳጅ፣ ጽናት እና ጀግንነት የሀገሩን እና የሕዝቡን ሉዓላዊነት ያስጠብቃል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck