በከተማዋ የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንደሚጠናቀቁ የደሴ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።

341

ደሴ:የካቲት 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 35ኛ መደበኛ ጉባዔ ተካሂዷል። የምክር ቤት አባላቱ በከተማዋ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ሥራዎች አበረታች መኾናቸውን ገልጸዋል።

በከተማዋ የተጀመሩትን ተስፋ ሰጪ ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ያነሱት አባላቱ፤ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበጀት ዓመቱ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተለይም የኅብረተሰቡ የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ለሕዝቡ ቃል የተገቡ ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንደሚጠናቀቁም ነው አቶ ሳሙኤል የገለጹት።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የደሴ ከተማ ተወካይ የተከበሩ ዶክተር ማሕተመ ሃይሌ በበኩላቸው ሕዝቡ ካለው የልማት ጥያቄ አንጻር በዚህ ዓመት መልካም ተግባራት መኖራቸውን ገልጸው ኹሉም ለዚህ ተባባሪ እንዲሆን ጠይቀዋል።

ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የመልካም አሥተዳደር እና የልማት ችግሮችን ለመፍታት የምክር ቤት አባላት ሕዝባዊ ውክልናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል” የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔ
Next articleፈተና ጥሪ ማስታወቂያ