“የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራርን እንዲተገብሩ አድርጓል” የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል

143

አዲስ አበባ: የካቲት 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የፋይናንስ ተቋማት የአምራች ኢንዱስትሪውን በመደገፍ በኩል የሚጫወቱት ሚና በሚል ርእሰ ጉዳይ በአዲስ አበባ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በመድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ለወራት ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራርን እንዲተገብሩ አድርጓል ብለዋል።

በዛሬው መድረክ የፋይናንስ ተቋማት በዘርፉ የሚስተዋለውን የፋይናንስ እጥረት ተወያይቶ መፍትሔ ለማስቀመጥ ሚናው የጎላ ይኾናል ብለዋል።

ዘርፉ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት፣በሂደቱ ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለማቃለል እንዲያግዝ የተጀመረው የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራርና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጎንደር ከተማ በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባው የዳቦ ፋብሪካ ተመርቆ ሥራ ጀመረ።
Next article“የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ዓላማ ሰላም የኾነችና ለዜጎች የምትመች ኢትዮጵያን መገንባት ነው” ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም