ዜና ሹመት ‼️

889

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ለተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሠረት፦
1. ወይዘሮ ሰላማዊት ዓለማየሁ በቀለ=>የርዕሰ መሥተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣

2.አቶ ቀለሙ ሙለነህ እምሩ=>የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣

3. አቶ ዘውዱ ማለደ በላይ=>የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣

4. ዲያቆን ተስፋው ባታብል ቢታው=>የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር፣

5. ወይዘሮ ንጹሕ ሽፈራው ቸኮል=>የሴቶች ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣

6. አቶ ወርቁ ያየህ ጨቅሌ=>የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር፣

7. አቶ ማግኘት መልካሙ ሐበሻ=>የአብክመ መሬት ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣

8. አቶ ዘውዱ ሙጨ አምባው=>የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣

9. አቶ ሱለይማን እሸቱ ባሻ=>የአብክመ ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣

10. አየለ አናውጤ ገሰሰ (ዶ.ር) =>የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣

11. ወይዘሮ የለምሽዋ በቀለ ወልዴ=>የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ

12. አቶ ጌትነት አማረ ገብረሕይዎት=>በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ባለስልጣን ኃላፊ፣

13. አቶ ታደሰ ይርዳው ሞላ=>የመንገድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣

14. ተስፋዬ ተገኘ ፈሩህ (ዶ.ር)=> በመምሪያ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ፕላን ኢኒስቲትዩት ባሕርዳር ቅርጫፍ አስተባባሪ፣

15. ወይዘሮ እሌኒ አባይ ጀምበሬ=>የሴቶች ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ፣

16. አቶ ስማቸው ደምለው ከበደ=>የወጣቶች ጉዳይ አማካሪ ኹነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥተዋል።

መረጃው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያን በፊዚክሱ ዘርፍ አንድ እርምጃ ማራመድ እፈልጋለሁ” በሀገር አቀፍ ፈተና 658 ነጥብ ያስመዘገበው ተማሪ ታዳኤል ሐይለመለኮት
Next article“የትናንት ዘር፣ የዛሬ ፍሬ፣ የነገ ስንቅ!” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ