አቶ ደመቀ መኮንን ለቻይና አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሥተላለፉ።

147

ባሕር ዳር :ጥር 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለቻይና አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አሥተላልፈዋል።

አቶ ደመቀ በየእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው፣ “አዲሱ ዓመት ለቻይና ሕዝብ የደስታ እና የብልጽግና እንዲሆን ከልቤ እመኛለሁ” ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

“አዲሱን ዓመት በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት የበለጠ ከፍ ለማድረግ እንደምንጠቀምበት ሙሉ እምነት አለኝ” ሲሉም አክለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በመስክ ምልከታው የተፈናቃዮችን ወቅታዊ ኹኔታም ይመለከታል ተብሏል።
Next articleበኩር ጋዜጣ ጥር 15/2015 ዓ.ም ዕትም