“እነርሱ ለእኛ ይሄንን ሲያደርጉ፣ እኛ ለገዛ ወገኖቻችን ከዚህ በላይ እንድናደርግ ትምህርት ይሆነናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

164

ባሕር ዳር: ጥር 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደተመለከቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ለዚህም 17682 ካሬ ሜትር መሬት ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬት መንግሥት መሠጠቱን ገልጸዋል።
የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት መንግሥት ላደረገው መልካም ተግባርም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም አመሰግናለሁ ብለዋል።

“ለጊዜው መገልገያ የሚሆነው ቤተ ክርስቲያን እየተጠናቀቀ ነው፤ የጥምቀት በዓል በቦታው እንዲከበር የሚቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቃል ተገብቶልናል” ነው ያሉት።
መሰል ቦታዎች የታሪክና የዲፕሎማሲያችን ትምህርቶች ናቸው። እነርሱ ለእኛ ይሄንን ሲያደርጉ፣ እኛ ለገዛ ወገኖቻችን ከዚህ በላይ እንድናደርግ ትምህርት ይሆነናል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleʺ ጃን ተከል ኀያላኑ ያረፉበት፣ ሊቃውንቱ የተሰባሰቡበት”
Next articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ