
አዲስ አበባ :ጥር 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዘንድሮ የጥምቀት በዓልን አስመልክተው መግለጫ የሰጡት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ናቸው።
ከከተራ ጀምሮ የሚከበረውን የኢየሱስ ክርስቶስን የጥምቀት በዓል ከአንድ ሺህ አምስት መቶ አመት ጀምሮ በአደባባይ ሲከበር የቆየ በዓል ነው ብለዋል ብፁዕነታቸው ።
ብፁዕነታቸው እንዳሉት መጽሐፍ ቅዱስ በጥምቀት ዳግም መወለድን፣ መታደስን አገኘን ይላል ብለዋል። ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ተነስተው ኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ በማድረግ በባህረ ጥምቀት ስርዓቱን እንደሚያከናውኑም አስረድተዋል።
በዓለ ጥምቀቱ በአዲስ አበባ ከተማ በ12 ክፍለ ከተሞች ፤ በ83 የተለያዩ ቦታዎች ይከበራል።
ወይብላ ማርያምና አምስቱ አድባራት በተለመደው ቦታቸው እንዲያከብሩ ከመንግስትና ከከተማዋ ከንቲባ ጋር በመነጋገር ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል ብፁዕ አቡነ ሄኖክ።
የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ ፅዋ ማኅበራት እንዲኹም ኅብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሥራት በዓሉ በሰላም እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የጥምቀት በዓል ዓለም ዓቀፋዊ በዓል እንደመኾኑ መጠን የውጪ ሀገራት ቱሪስቶች የሚገኙበት በመኾኑ፤ ኹሉም የሃይማኖት ተቋማት የሀገሪቱን ገፅታ በመገንባት ሂደት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- አየለ መስፍን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!