
ጎንደር:ጥር 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የማእከላዊ ጎንደር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ ለ2015 ዓ.ም የጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ እና የመልካም ምኞት መልእክት አስተላልፈዋል።
ጥምቀት የእያንዳንዱ ክርስቲያን የመዳን ምልክት ነው ያሉት ብጹዑ አቡነ ዮሐንስ የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በሰላም ፣በፍቅር ፣በአንድነትና በመተባበር ማክበር ይገባናል ብለዋል።
የሳይጣንን ሥራ ለማፍረስ፣ከሃጢያት የነጻ አዲስ ሕይወት የተሰጠበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ።
የጥምቀትን በዓል ለማክበር ከየዓለሙ ዳርቻ የሚመጡ እንግዶች ሰላማዊ አካባቢና ሁኔታን ይፈልጋሉ እና በሰላም አክብረው እንዲመለሱ ሁሉም ኀላፊነቱን መወጣት ይገባዋል ነው ያሉት።
በዓሉ የሰላም ፣የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲኾንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ:-ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!