
ባሕር ዳር፡ ጥር 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2050 የካርበን ልቀትን ዜሮ ለማድረስ ግብ አስቀምጣ በትኩረት እየሠራች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፤ በዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በሚመክረው15ኛው የአቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ “ሰስቴኔቢሊቲ” ጉባዔ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ በርካታ ሥራዎች እያከናወነች መኾኑን አብራርተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!