አቶ ደመቀ መኮንን በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ።

277

ባሕርዳር፡ ጥር 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጁኒፐር ግላስግላስ ብርጭቆ ፋብሪካ እና ሌሎችንም በከተማዋ የሚገኙ ኢንደስትሪዎችን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተንቀሳቅሰው ጎብኝተዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያሳየው ፤ከጉብኝት በኋላም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ባለሀብቶች ጋር ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ወይይት ተካሂዷል።

በደብረ ብርሃን ከተማ ብሎም በዞኑ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ምን ምን እንደሆኑ በዝርዝር ቀርቦ ምክክር ተካሂዷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleገብርየ ገብርየ የጦር መኮነኔ፣ አሽከሬም አይደለህ ወንድሜ ነህ ለኔ!
Next article“አዝማሪነት ነቃሽነት እና የወደፊቱን ጠቋሚነት ነው” የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ