“ጃንሜዳን በህብረት ለጥምቀት” በሚል መሪ ቃል የታቦታቱን ማደሪያ የማፅዳት ስነስርዓት ተካሄደ።

173

ባሕር ዳር: ጥር 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ጃንሜዳን በህብረት ለጥምቀት ” በሚል መሪ ቃል የታቦታቱን ማደሪያ የማፅዳት ስነስርዓት ተካሄደ።

የፊታችን ረቡዕ እና ሀሙስ ለሚከበሩት የከተራ እና ጥምቀት በዓል በጃንሜዳ የታቦታቱን ማደሪያ የእስልምና እና ክርስትና እምነት ተከታዮች በጋራ አፅድተዋል።

በፅዳት መርሃ ግብሩ ላይ “አብሮነትና ወንድማማችነት ለጥምቀት ድምቀት፣ ፅዳትና ውበት ለጥምቀት” እንዲሀም “መጥረጊያችንን አንስተን የታቦታቱን ማደሪያዎች ጽዱ እናደርጋለን” የሚሉ መልዕክቶችን ተሳታፊዎች አስተላልፈዋል።

“ሁላችንም በዓሉ የበለጠ እንዲደምቅና ለዓለም የኢትዮጵያን ገፅታ እንዲያሳይ ለማድረግ ስንል ምንም ልዩነት ሳይዘን እዚህ ተገኝተናል” ሲሉ የፅዳት መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

“ኢድ አልፈጥርን በስታዲየም ስናከብር ሁሉም ቤተ ዕምነቶች አፅድተዋል አሁንም ጥምቀት የሚከበርበትን ቦታ ሁላችንም የጋራችን ነውና እናፀዳለን” ያሉት ደግሞ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የተወከሉት ሼክ ሰማ መሀመድ ናቸው።

አክለውም “ይህ በዓል የአንድ ሀይማኖት በዓል ብቻ አይደለም፤ የሁላችንም ቅርስና ሀብት በመሆኑ በሰላም እንዲከበርም የበኩላችንን እናደርጋለን” ብለዋለ። ዘገባው የኤፍ ቢ ሲ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ገለፀ።
Next article“በበጌምድር ያለ ግብር በሰማይ ያለ ዱር”