
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎንና እና ከጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ፥ ጥልቅ እና ፍሬያማ ውይይታችን ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ጋር ያላትን ጠንካራ እና የቆየ ግንኙነትን የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት እያከናወነች ያለችውን ዘርፈ ብዙ ማሻሻያ፣ ቁልፍ ውጤቶችንና ተያያዥ ችግሮችን አካፍለዋል።
ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ጋር ያላት ግንኙነት ለበርካታ ዐሠርት ዓመታት መቆየቱንም ነው ያነሱት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ፥ ባለፉት አራት ዓመታት ከሁለቱም ሀገራት ለተደረገው ያልተቋረጠ ድጋፍ አመስግነዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮችም ለውጡን ለማስቀጠል የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።