
ባሕርዳር: ጥር 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሔ የሚሰጥ የኢንቨስትመንት ፎረም በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው::
“ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ መልእክት በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሔ መስጠት የሚያስችል የኢንቨስትመንት ፎረም በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ ዘርፉ የተሻለ ገቢ እንዲያመነጭ የሚያስችል ፎረም ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በክልሉ ለሚያለሙ ባለሀብቶች ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠር በፎረሙ ላይ አንስተዋል ፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ካሳሁን እንቢአለ የኢንቨስትመንት ፎረሙ በባለፉት ሁለት ዓመታት የተቀዛቀዘው የኢንቨስትመንት ዘርፍን ሊያነቃቃ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
በከተማው ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከ7 መቶ በላይ ባለሀብቶች ማልማታቸውን አቶ ካሳሁን አንስተዋል። የክልሉ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ በክልሉ ሠፊ የኢንቨስትመንት ሀብት መኖሩን ተናግረዋል። ክልሉ 2 ሺህ 500 ባለሀብቶች ያሉበት፣ 500 ሺህ ሥራ ፈላጊዎች የሥራ እድል መፈጠሩን ኀላፊው ጠቁመዋል፡፡
አቶ እንድሪስ እንዳሉት ከባለፈው የኢንቨስትመንት ፎረም በኋላ ወደ ሥራ ያልገቡ 178 ፕሮጀክቶች እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡
ዘጋቢ:- ገንዘብ ታደሰ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!