“በግማሽ ዓመቱ 33 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብስበናል” ኢትዮ ቴሌኮም

64

አዲስ አበባ: ጥር 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወር ሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው በበጀት ዓመቱ የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም 33 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲኾን የዕቅዱ 96 በመቶ ማሳካቱን ተነግሯል።

ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ19 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን በብር 5 ነጥብ 62 ቢሊዮን ብር እድገት ተገኝቷል።

ከትርፍ አንፃር 8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ተገኝቷል። በባለፈው በጀት ዓመት አጠቃላይ 9 ቢሊዮን ትርፍ የተገኘ እንደነበር ያስታወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት በዚህ ግማሽ ዓመት የተገኘው ትርፍ አምና በዓመቱ ከተገኘው ተቀራራቢ ነው ለዚህም ለውድድር ገብያው አስቀድሞ መዘጋጀታችን፣ ችግሮችን በፅናትና በትግስት መሻገራችን እንዲሁም በወጪ መቆጠብ ስትራቴጂ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ መቆጠቡ ለስኬቱ አስተዋፅኦ አድርጓል።

ዘጋቢ:- ማርታ ጌታቸው

ተጨማሪ ካለ እጨምራለሁ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕርዳር ተገኝተው የሰሜን ምዕራብ እዝን እየጎበኙ ነው።
Next articleየአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለቀጣይ ሥራው ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከአጋር አካላት ጋር መከረ፡፡