
ባሕር ዳር: ጥር 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕርዳር ተገኝተው ምዕራብ እዝን እየጎበኙ ነው። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በባሕርዳር የሚገኘውን የሰሜን ምዕራብ እዝ ደረጃ ሦስት ሆስፒታልን ጎብኝተዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊውጂን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር ጄኔራል መኮንኖች ተገኝተዋል።
ሀገርን ለማጽናት የተዋደቁ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ሕዝባችንን ይዘን የማንፈፅመው ተልዕኮና የማንወጣው ግዳጅ የለም፣ የተሰዋነው እና የቆሰልነው ለሕባችን ደኅንነት ነው፣ ለሕዝብ አንድነትና ክብር ነው።
አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩዋትን ሀገር በደማችን እና በአጥንታችን አስከብረን ለትውልድ እናስተላልፋለን ብለዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!