አምባሳደር ምሥጋኑ አረጋ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ።

211

ባሕርዳር፡ ጥር 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አምባሳደር ምሥጋኑ አረጋን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አድርገው ሾመዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ ከአሁን በፊት በኳታር እና በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ማገልገላቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

 

 

Previous article“ጎንደር የጥምቀትን በዓል ለማክበር አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጋለች” የከተማዋ ከንቲባ
Next articleየኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለውጭ ባንኮች ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ገለፀ።