
ባሕር ዳር: ጥር 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ቡድን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ መሪነት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ቡድን መሪ የሆኑት ዶ/ር አብዱልአዚዝ ሰርሃን በኢትዮጵያ ተክስቶ በነበረው ጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም እና ለኅብረተሰቡ ድጋፍ ለማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው በውይይቱ ውቅት አንሥተዋል።
ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የተካሄደው ውይይቱ፣ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር በሰላም እና በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!