የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል 1 የማሻሻያ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ ።

169

ባሕር ዳር፣ ታኅሣሥ 26/2015 (አሚኮ) የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ በረራ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ሲካሄድለት የነበረው የማሻሻያ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል አንድ በግንባታ ላይ በነበረበት ወቅት የሀገር ውስጥ መንገዶች የዓለም አቀፍ በረራዎች ተጓዦች የሚጠቀሙበትን ተርሚናል ሁለት ሲጠቀሙ ቆይተዋል።

በቻይናው ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) ግንባታው የተከናወነው ተርሚናል አንድ በ16 ሺህ 689 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ መሆኑን ከግንባታው ተቋራጭ የተገኘውን መረጃ ጠቅሶ ኤ ቢ ሲ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበዴንማርክ የነበሩ ጥንታዊ የግእዝ መድብሎች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አስታወቀ።
Next article“አሸንፈን ሠላምን፣ አንድነትንና ልዕልናን ማምጣት እንድንችል ኢትዮጵያ አፋርን መሆን አለባት” ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት