በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ወደ መቀሌ አቀና።

480

የልኡካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው።

የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቀሌ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልኡክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑ ታምኖበታል።

በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም ተካትተዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Previous articleበኩር ጋዜጣ – ታኅሣሥ 17/2015 ዓ.ም ዕትም
Next articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Mudde 15/2015