አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በደሴ ከተማ የሚያስገነባው ባለ 12 ወለል የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሕንፃ ግንባታን አስጀመረ።

171

ደሴ፡ ታኅሣሥ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ በሚኒስቴር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ማዕከል ኀላፊ ዛዲግ አብረሃ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ፣ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የሕዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ እና የአሚኮ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ የሺጥላ፣ የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥየና የቦርድ አባላት፣ የደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች የሥራ ኀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥየ “ከ544 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረግበታል የተባለው የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሕንፃ ግንባታ በ 3 ዓመት ከ 4 ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል” ብለዋል።

የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታደሰ ግርማ የአሚኮን የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሕንፃ ከተባለው ጊዜ ቀድሞ ለማጠናቀቅ እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል ።

ዘጋቢ:- ከድር አሊ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሀገር አቀፍ ደረጃ ዕድሜያቸው ከ 9 ወር እስከ 5 ዓመት የኾኑ ከ15 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሕጻናት የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት በዘመቻ እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleበሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚፈጸሙ የሥነ ምግባር ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ።