በሀገር አቀፍ ደረጃ ዕድሜያቸው ከ 9 ወር እስከ 5 ዓመት የኾኑ ከ15 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሕጻናት የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት በዘመቻ እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

226

አዲስ አበባ፡ ታኅሣሥ 13/2015 ዓ.ም በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከ5 ዓመት በታች ለኾኑ ለ520 ሺህ ህጻናት የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት በዘመቻ እንደሚሰጥ የአዲስ አበበ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ ሥነ- ሥርዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ እየተካሄደ ነው ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደረጃ ከ63 ሺህ በላይ ሕጻናት በዘመቻ እንደሚከተቡ ተገልጿል። ክትባቱ በአዲስ አበባ ደረጃ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ይሰጣል ተብሏል ።

በኢትዮጵያ 14 የክትባት አይነት ይሰጣል። ከዚህ ውስጥ የኩፍኝ ክትባት ዋና መኾኑን የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ•ር ደረጄ ዱጉማ ገልጸዋል።

በቀጣይ ሦስት እና አራት አመታት ተፈላጊውን ውጤት እስከሚመጣ ዘመቻ ይቀጥል ብለዋል ሚኒሲቴር ዴኤታው።

ዘጋቢ፡- ዳንኤል መላኩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleወሎ የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባሕል ኮንፈረንስ እና ፌስቲቫል በአዲስ አበባ እና ደሴ ከተሞች ይካሄዳል፡፡
Next articleአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በደሴ ከተማ የሚያስገነባው ባለ 12 ወለል የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሕንፃ ግንባታን አስጀመረ።