የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ መደበኛ ጉባዔውን ያካሂዳል።

133

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባዔ የምክር ቤቱን 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባኤ መርምሮ በማፅደቅ የሚጀምር ይሆናል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላትን ሹመት መርምሮ የሚያፀድቅ ሲሆን፤ በምክር ቤቱ አዳዲስ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ምደባን አስመልክቶ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይም ተወያይቶ ምደባውን የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡

የመንግስትና የግል አጋርነት እንዲሁም የብሔራዊ ክፍያ ስርዓት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚያቀርበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ አዋጁን በማፅደቅ የዕለቱን ጉባዔ የሚያጠናቅቅ ይሆናል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ የዐይን ባንክ እስካሁን 1 ሺህ 9 መቶ በላይ ሰዎች የዐይን ብርሃናቸው እንዲበራላቸው ማድረጉ ተገለጸ።
Next articleምሁራን በእውቀት ላይ የተመሠረተ የመፍትሔ ሀሳብ በማፍለቅ በአገረ-መንግሥት ግንባታ ላይ የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።