
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ዓመታዊ ግምገማውን በባሕር ዳር እያካሄደ ነው። በመክፈቻው ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጀግኖች አርበኞች የውጪ ወራሪዎችን በራሳቸው ትጥቅና ስንቅ ታግለው ማሸነፋቸውን ተናግረዋል። ዛሬም ቢኾን አርበኞች የአሁኑን ትውልድ እያስተማሩ ይገኛሉ ብለዋል።
የሀገር ምልክት የኾኑትን አርበኞች ማክበርና መደገፍ እንደሚገባ ያስገነዘቡት ርእሰ መሥተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ መንግሥት ብቻ ሳይኾን ግለሰቦችም ኾኑ ባለ ሀብቶች ተገቢውን ድጋፍ ሊያበረክትላቸው እንደሚገባ ጠይቀዋል።
የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርን ለመደገፍ መንግሥት የበኩሉን ጥረት እንደሚያደርግ ርእሰ መሥተዳደሩ አረጋግጠዋል።
የክልሉ መንግሥት ለጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር የሚኾን አደባባይ በባሕር ዳር እንደሚሰይም ቃል ገብተዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!