ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍና ለደን መልሶ ልማት ላደረገችው አስተዋጽዖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አገኘች።

254

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “አፍሪካ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት” በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንት እና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ስታስጀምር፣ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢልዮን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷ የሚታወስ ነው።

ሀገሪቱም ከታቀደው ግብ በላይ በመላ ሀገሪቱ 25 ቢልዮን ችግኞች በመትከል የአራት ዓመታት ዕቅዷን አሳክታለች። በዚህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለደን መልሶ ልማት ላደረገችው አስተዋጽዖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝታለች።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleʺሞተውም ይኖራሉ፣ አልፈውም ያኮራሉ”
Next articleየእኛ ሰው በሞሮኮ!