
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኩፍኝ ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ ታህሣስ 13 ጀምሮ የሚሰጥ በመሆኑ እስከ 5 ዓመት የእድሜ ክልል ያሉ ህፃናት እንዲከተቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኩፍኝ በሽታ መድኃኒት ክትባት ማሠራጨቱን በመድኃኒት ክምችት አያያዝ አስተዳደር የክትባት መድኃኒት ተጠሪ አቶ ሀብታሙ አለማየሁ ገልጸዋል፡፡
የክትባት መድኃኒቱ በመላው የኢትዮጵያ ክልሎች የሚካሄድ ሲሆን በዚህም 16 ሚሊየን 298 ሺህ በላይ ሕፃናትን መከተብ እንደሚል ተመላክቷል፡፡
ክትባቱ ከታህሣስ 13 ጀምሮ እንደሚሠጥና እስከ 5 ዓመት የእድሜ ክልል ያሉ ህፃናት እንዲከተቡ ጥሪ መቅረቡን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኩፍኝ በሽታ በትንፋሽ ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፍ ነው፡፡
ይህ በሽታም ሕፃናትን እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል በመሆኑ ማኅበረሰቡ ይህንን በመገንዘብ ሕፃናቱን በወቅቱ እንዲያስከትብ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!