
ጎንደር፡ ሕዳር 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምርምር ማዕከሉ በሽታን የሚቋቋሙ ፣ ከአካባቢ አየር ንብረት ጋር ተስማሚ የኾኑና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የሽንብራ፣ የምስርና፣ የባቄላ ሰብልን
ከ68 ሄክታር በላይ መሬት አርሶ አደሮች እንዲያለሙ እየሠራ መኾኑን የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ምንተስኖት ወርቁ ተናግረዋል ።
በዳባትና በወገራ ወረዳዎች ምርታቸው እየቀነሰ የመጣውን የሽንብራና የምስር ሰብልን በተሻሻሉ ዝርያ ባላቸው ዘሮች በመተካት እንዲለሙ እየተደረገ መኾኑንም ኀላፊው ተናግረዋል ።
የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል ከአዝዕርትና ከጥራጥሬ ሰብል በተጨማሪ የእንስሳትን ዝርያ ለማሻሻል እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ዘጋቢ:- ጳውሎስ አየለ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ መረጃ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck