
ባሕር ዳር: ሕዳር 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በክልሉ የግብርና ዘርፉን ለማዘመን የሚረዱ ለተለያዩ የግብርና ሥራዎች የሚውሉ ማሽነሪዎችን ነው ከአምባሰል የንግድ ሥራዎች ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተረከበው።ማሽነሪዎቹ 298 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው ናቸው።
ቢሮው ከአሁን በፊትም በተለያዩ ጊዜያት ትራክተሮችን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ሜካናይዜሽንን ሊያሳድጉ የሚችሉ ማሽነሪዎችን በማስገባት አገልግሎት ላይ እንዲውሉ አድርጓል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ዛሬ
👉37 ትራክተሮች
👉2 ኮምባይነሮች
👉3 የሳር ማጨጃ
👉5 ዘር መዝሪያ
👉2 ኬሚካል መርጫ
👉14 ማረሻ
👉7 በመስመር መዝሪያ
👉11የትራክተር ጋሪ
👉2 መሬት ማስተካከያ
👉4 ሲኖ ትራክ
👉29 ሁለገብ መፈልፈያ
👉4 የበቆሎ መፈልፈያ ማሽነሪዎችን ከአምባሰል የንግድ ሥራዎች ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ተረክቧል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ መረጃ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck