
ባሕር ዳር: ሕዳር 29/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ሊቀመንበርነትን መረከቧን ተከትሎ በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት እንዲጠናከር ቁርጠኛ ናት ብለዋል።
ሊቀመንበርነቱን ከዴሞክራቲክ ሪፐፕሊክ ኮንጎ ፖሊስ አዛዥ ዲዶኔ አሙሊ ባሂግዋ ለተረከቡት ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንኳን ደስ አለዎት ያሉት ፕሬዝዳንቷ በቀጣናው እየተበራከተ የመጣውን የአደንዛዥ ዕፅ፣ የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል እና ሽብርተኝነትን በመከላከል በትጋት በመሥራት ለውጥ እንደሚያመጡ አምናለሁ ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የኢትዮጵያን ፖሊስ ታሪክ የሚያሳይ አውደ ርእይ በአፍሪካ ኅብረት መርቀው ከፍተዋል። በአውደ ርእዩ የሀገራችን ፖሊስ አሁን እስካለው ደረጃ የሚጠቀምባቸውን የደንብ ልብሶች ጫማዎች፣ የትከሻ ማዕረጎች፣ መለዮዎች እንዲሁም የፖሊስ ኦርኬስትራ ባንድ መሳሪያዎች እየተጎበኙም ነው።
ኢትዮጵያ የፖሊስ አገልግሎትን ለማጠናከር የሠራችው ሥራ እና ከአህጉሩ እና ከዓለማቀፍ ግንኙነት አኳያ የሠራችውን ሥራዎች የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርእይም የመርኃ ግብሩ አካል ነው።
ዘጋቢ፡- ማርታ ጌታቸው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ መረጃ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck