
ባሕር ዳር: ሕዳር 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለያዩ ጥቃቶችን በንጹሃን ዜጎች ላይ እየፈፀመ እንደሚገኝና መንግሥት ሰላማዊ አማራጭን ሲከተል ቢቆይም አሁን ላይ ሕግን እንደሚያስከብር የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አስታውቀዋል። ችግሩን ዘላቂነት ባለው መንገድ ለመፍታት እንደሚሠራም ተናግረዋል።
ለአራት ቀናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከረው የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅምን በውጤት ፈተናን በስኬት በሚል መሪ መልዕክት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው ቀዳሚ አጀንዳው ካደረጋቸው ጉዳዮች መካከል የሀገሪቱ ሰላም አንደኛው ነው።
በተለይም ከህወሓት ጋር የተደረሰው የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያመላከተ በመሆኑ ለስምምነቱ ትግበራ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አቋም መያዙን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ተናግረዋል፡፡
የሰላም ስምምነቱ ለሀገረ መንግሥት ግንባታው ፋይዳው የላቀ መሆኑንም አንስተዋል።
መንግሥት በመላው ኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም እንዲመጣ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ግን ዛሬም በእኩይ ተግባሩ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡
ቡድኑ የመላው ኢትዮጵያውያን ጠላት በመሆኑ በጋራ በመሆን መመከት እንደሚገባ እና ችግሩን በዘላቂነት መፍታት እንደሚያስፈልግ አባላቱ ተናግረዋል። ዘገባው የፋብኮ ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ መረጃ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck